1 ሳሙኤል 24:16-18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ዳዊት ይህን ተናግሮ ሲጨርስ ሳኦል “ልጄ ዳዊት፣ ይህ የአንተ ድምፅ ነው?”+ አለው። ከዚያም ሳኦል ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ። 17 ዳዊትንም እንዲህ አለው፦ “አንተ መልካም ስታደርግልኝ እኔ ግን ክፉ መለስኩልህ፤ ስለሆነም አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።+ 18 አዎ፣ ይሖዋ እኔን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህም ሳትገድለኝ በመቅረት ለእኔ ያደረግከውን መልካም ነገር ይኸው ዛሬ ነገርከኝ።+ 1 ሳሙኤል 26:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ሳኦልም መልሶ እንዲህ አለው፦ “በእርግጥ ኃጢአት ሠርቻለሁ።+ ልጄ ዳዊት ሆይ፣ ከእንግዲህ ምንም ጉዳት ስለማላደርስብህ ተመለስ፤ ምክንያቱም በዛሬው ዕለት ሕይወቴን* ውድ አድርገህ+ ተመልክተሃታል። በእርግጥም የሞኝነት ድርጊት ፈጽሜአለሁ፤ ትልቅ ስህተት ሠርቻለሁ።”
16 ዳዊት ይህን ተናግሮ ሲጨርስ ሳኦል “ልጄ ዳዊት፣ ይህ የአንተ ድምፅ ነው?”+ አለው። ከዚያም ሳኦል ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ። 17 ዳዊትንም እንዲህ አለው፦ “አንተ መልካም ስታደርግልኝ እኔ ግን ክፉ መለስኩልህ፤ ስለሆነም አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።+ 18 አዎ፣ ይሖዋ እኔን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህም ሳትገድለኝ በመቅረት ለእኔ ያደረግከውን መልካም ነገር ይኸው ዛሬ ነገርከኝ።+
21 ሳኦልም መልሶ እንዲህ አለው፦ “በእርግጥ ኃጢአት ሠርቻለሁ።+ ልጄ ዳዊት ሆይ፣ ከእንግዲህ ምንም ጉዳት ስለማላደርስብህ ተመለስ፤ ምክንያቱም በዛሬው ዕለት ሕይወቴን* ውድ አድርገህ+ ተመልክተሃታል። በእርግጥም የሞኝነት ድርጊት ፈጽሜአለሁ፤ ትልቅ ስህተት ሠርቻለሁ።”