1 ሳሙኤል 15:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ከዚያም ሳሙኤል እንዲህ አለ፦ “ይሖዋን ይበልጥ የሚያስደስተው የትኛው ነው? የሚቃጠሉ መባዎችንና መሥዋዕቶችን+ ማቅረብ ወይስ የይሖዋን ቃል መታዘዝ? እነሆ፣ መታዘዝ ከመሥዋዕት፣+ መስማትም ከአውራ በግ ስብ+ ይበልጣል፤ 23 ምክንያቱም ዓመፀኝነት+ ሟርት+ ከመፈጸም አይተናነስም፤ እብሪተኝነትም ቢሆን ከጥንቆላና ከጣዖት አምልኮ* ተለይቶ አይታይም። አንተ የይሖዋን ቃል ስላልተቀበልክ+ እሱም የአንተን ንግሥና አልተቀበለውም።”+ ምሳሌ 15:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይሖዋ የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤+የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል።+ ኢሳይያስ 1:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?”+ ይላል ይሖዋ። “የሚቃጠሉ የአውራ በግ መባዎችና+ የደለቡ እንስሳት ስብ+ በቅቶኛል፤በወይፈኖች፣+ በበግ ጠቦቶችና በፍየሎች+ ደም+ ደስ አልሰኝም።
22 ከዚያም ሳሙኤል እንዲህ አለ፦ “ይሖዋን ይበልጥ የሚያስደስተው የትኛው ነው? የሚቃጠሉ መባዎችንና መሥዋዕቶችን+ ማቅረብ ወይስ የይሖዋን ቃል መታዘዝ? እነሆ፣ መታዘዝ ከመሥዋዕት፣+ መስማትም ከአውራ በግ ስብ+ ይበልጣል፤ 23 ምክንያቱም ዓመፀኝነት+ ሟርት+ ከመፈጸም አይተናነስም፤ እብሪተኝነትም ቢሆን ከጥንቆላና ከጣዖት አምልኮ* ተለይቶ አይታይም። አንተ የይሖዋን ቃል ስላልተቀበልክ+ እሱም የአንተን ንግሥና አልተቀበለውም።”+
11 “የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?”+ ይላል ይሖዋ። “የሚቃጠሉ የአውራ በግ መባዎችና+ የደለቡ እንስሳት ስብ+ በቅቶኛል፤በወይፈኖች፣+ በበግ ጠቦቶችና በፍየሎች+ ደም+ ደስ አልሰኝም።