1 ሳሙኤል 16:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከአገልጋዮቹም አንዱ እንዲህ አለ፦ “የቤተልሔሙ ሰው የእሴይ ልጅ በገና የመደርደር ጥሩ ችሎታ እንዳለው አይቻለሁ፤ እሱም ደፋርና ኃያል ተዋጊ ነው።+ ደግሞም አንደበተ ርቱዕና መልከ መልካም+ ሲሆን ይሖዋም ከእሱ ጋር ነው።”+ 19 ከዚያም ሳኦል ወደ እሴይ መልእክተኞችን ልኮ “በጎች የሚጠብቀውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ” አለው።+ 1 ነገሥት 7:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ንጉሥ ሰለሞን መልእክተኛ ልኮ ኪራምን+ ከጢሮስ አስመጣው። 14 ኪራም ከንፍታሌም ነገድ የሆነች የአንዲት መበለት ልጅ ነበር፤ አባቱ የጢሮስ ሰው ሲሆን የመዳብ ሥራ ባለሙያ+ ነበር፤ ኪራም ከማንኛውም የመዳብ* ሥራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችሎታ፣ ማስተዋልና+ ልምድ ነበረው። በመሆኑም ወደ ንጉሥ ሰለሞን መጥቶ ሥራዎቹን ሁሉ አከናወነለት።
18 ከአገልጋዮቹም አንዱ እንዲህ አለ፦ “የቤተልሔሙ ሰው የእሴይ ልጅ በገና የመደርደር ጥሩ ችሎታ እንዳለው አይቻለሁ፤ እሱም ደፋርና ኃያል ተዋጊ ነው።+ ደግሞም አንደበተ ርቱዕና መልከ መልካም+ ሲሆን ይሖዋም ከእሱ ጋር ነው።”+ 19 ከዚያም ሳኦል ወደ እሴይ መልእክተኞችን ልኮ “በጎች የሚጠብቀውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ” አለው።+
13 ንጉሥ ሰለሞን መልእክተኛ ልኮ ኪራምን+ ከጢሮስ አስመጣው። 14 ኪራም ከንፍታሌም ነገድ የሆነች የአንዲት መበለት ልጅ ነበር፤ አባቱ የጢሮስ ሰው ሲሆን የመዳብ ሥራ ባለሙያ+ ነበር፤ ኪራም ከማንኛውም የመዳብ* ሥራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችሎታ፣ ማስተዋልና+ ልምድ ነበረው። በመሆኑም ወደ ንጉሥ ሰለሞን መጥቶ ሥራዎቹን ሁሉ አከናወነለት።