1 ሳሙኤል 23:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 የሳኦል ልጅ ዮናታንም በሆሬሽ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት ሄደ፤ እሱም በይሖዋ ላይ ያለው ትምክህት እንዲጠናከር ረዳው።*+ ምሳሌ 15:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ሰው ትክክለኛውን መልስ በመስጠት* ሐሴት ያደርጋል፤+በትክክለኛው ጊዜ የተነገረ ቃልም ምንኛ መልካም ነው!+ ምሳሌ 16:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ደስ የሚያሰኝ ቃል እንደ ማር እንጀራ ነው፤ለነፍስ* ጣፋጭ፣ ለአጥንትም ፈውስ ነው።+