-
1 ነገሥት 3:11-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ከዚያም አምላክ እንዲህ አለው፦ “ይህን ነገር ስለጠየቅክ እንዲሁም ለራስህ ረጅም ዕድሜ* ወይም ብልጽግና አሊያም የጠላቶችህን ሞት* ሳይሆን የፍርድ ጉዳዮችን መዳኘት እንድትችል ማስተዋልን ስለጠየቅክ+ 12 የጠየቅከውን አደርግልሃለሁ።+ ከአንተ በፊት ማንም ሰው ያልነበረውን+ ከአንተ በኋላም ማንም ሰው የማያገኘውን ጥበበኛና አስተዋይ ልብ እሰጥሃለሁ።+ 13 በተጨማሪም በሕይወት ዘመንህ* ሁሉ ከነገሥታት መካከል አንተን የሚተካከል እንዳይኖር+ አንተ ያልጠየቅከውን+ ብልጽግናና ክብር+ እሰጥሃለሁ።
-