ዘፍጥረት 3:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከመሬት ስለተገኘህ+ ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ ላብህን እያንጠፈጠፍክ ምግብ ትበላለህ። አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ።”+ ምሳሌ 16:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ሠራተኛን የምግብ ፍላጎቱ* ተግቶ እንዲሠራ ያደርገዋል፤ረሃቡ* እንዲህ እንዲያደርግ ያስገድደዋልና።+