18 እኔ ያየሁት መልካምና ተገቢ የሆነ ነገር፣ ሰው እውነተኛው አምላክ በሰጠው አጭር የሕይወት ዘመን ሁሉ መብላቱና መጠጣቱ እንዲሁም ከፀሐይ በታች በደከመበትና በትጋት ባከናወነው ሥራ ሁሉ ደስታ ማግኘቱ ነው፤+ ይህ ብድራቱ ነውና።+ 19 ደግሞም እውነተኛው አምላክ ለሰው ሀብትና ቁሳዊ ንብረት+ ብሎም በእነዚህ ነገሮች የመደሰት ችሎታ ሲሰጠው ብድራቱን ተቀብሎ በትጋት በሚያከናውነው ሥራ መደሰት ይገባዋል። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።+