ዘዳግም 23:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “ለአምላክህ ለይሖዋ ስእለት ከተሳልክ+ ለመፈጸም አትዘግይ።+ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በእርግጥ ከአንተ ይፈልገዋል፤ አለዚያ ኃጢአት ይሆንብሃል።+ መዝሙር 76:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ለአምላካችሁ ለይሖዋ ተሳሉ፤ ስእለታችሁንም ፈጽሙ፤+በዙሪያው ያሉ ሁሉ በፍርሃት ስጦታቸውን ያምጡ።+ ማቴዎስ 5:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 “ከዚህም ሌላ በጥንት ዘመን ለነበሩት ‘በከንቱ አትማል፤+ ይልቁንም ለይሖዋ* የተሳልከውን ፈጽም’+ እንደተባለ ሰምታችኋል።