8 ስለዚህ ኪራም እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ሰለሞን ላከ፦ “የላክብኝ መልእክት ደርሶኛል። የአርዘ ሊባኖስና የጥድ ሳንቃዎች በማቅረብ ረገድ የፈለግከውን ሁሉ አደርጋለሁ።+ 9 አገልጋዮቼ ሳንቃዎቹን ከሊባኖስ ወደ ባሕሩ ያወርዷቸዋል፤ እኔም በባሕር ላይ ተንሳፈው አንተ ወደምትለኝ ቦታ እንዲደርሱ አንድ ላይ አስሬ እልካቸዋለሁ። እዚያም ሲደርሱ እንዲፈቱ አደርጋለሁ፤ ከዚያ ልትወስዳቸው ትችላለህ። አንተ ደግሞ በምላሹ የጠየቅኩህን ቀለብ ለቤተሰቤ ታቀርባለህ።”+