15 ኢየሱስም ይህን ሲያውቅ አካባቢውን ለቆ ሄደ። ብዙ ሰዎችም ተከትለውት ሄዱ፤+ እሱም የታመሙትን ሁሉ ፈወሳቸው፤ 16 ሆኖም የእሱን ማንነት ለሌሎች እንዳይገልጹ በጥብቅ አዘዛቸው፤+ 17 ይህን ያደረገው በነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፦
18 “እነሆ፣ የምወደውና ደስ የምሰኝበት+ የመረጥኩት አገልጋዬ!+ መንፈሴን በእሱ ላይ አደርጋለሁ፤+ ፍትሕ ምን ማለት እንደሆነም ለብሔራት ያሳውቃል።