ዘፍጥረት 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ሠራው፤+ በአፍንጫውም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፤+ ሰውየውም ሕያው ሰው* ሆነ።+ የሐዋርያት ሥራ 17:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ዓለምንና በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረው አምላክ፣ እሱ የሰማይና የምድር ጌታ+ ስለሆነ በእጅ በተሠሩ ቤተ መቅደሶች ውስጥ አይኖርም፤+ 25 በተጨማሪም ሕይወትንና እስትንፋስንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለሰው ሁሉ የሚሰጠው+ እሱ ስለሆነ የሚጎድለው ነገር ያለ ይመስል በሰው እጅ አይገለገልም።+
24 ዓለምንና በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረው አምላክ፣ እሱ የሰማይና የምድር ጌታ+ ስለሆነ በእጅ በተሠሩ ቤተ መቅደሶች ውስጥ አይኖርም፤+ 25 በተጨማሪም ሕይወትንና እስትንፋስንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለሰው ሁሉ የሚሰጠው+ እሱ ስለሆነ የሚጎድለው ነገር ያለ ይመስል በሰው እጅ አይገለገልም።+