ዘዳግም 32:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ምክንያቱም ቁጣዬ እሳት አቀጣጥሏል፤+እሱም እስከ መቃብር* ጥልቀት ድረስ ዘልቆ ይነድዳል፤+ምድርንና ምርቷን ይበላል፤የተራሮችንም መሠረት ያቃጥላል። ናሆም 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በቁጣው ፊት ማን ሊቆም ይችላል?+ የንዴቱን ትኩሳት ሊቋቋም የሚችልስ ማን ነው?+ ቁጣው እንደ እሳት ይፈስሳል፤ዓለቶችም ከእሱ የተነሳ ይፈረካከሳሉ።