የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 31:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ምክንያቱም ለአባቶቻቸው ወደማልኩላቸው+ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ በማስገባቸው ጊዜ በልተው ሲጠግቡና ሲበለጽጉ*+ ወደ ሌሎች አማልክት ዞር ይላሉ፤ እንዲሁም እነሱን ያገለግላሉ፤ እኔንም ይንቁኛል፤ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ።+

  • 2 ነገሥት 17:13, 14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 14 እነሱ ግን አልሰሙም፤ በአምላካቸው በይሖዋ እንዳላመኑት አባቶቻቸው እነሱም ግትሮች ሆኑ።*+

  • ነህምያ 9:26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+

  • ኢሳይያስ 1:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ኃጢአተኛ የሆነው ብሔር፣+

      ከባድ በደል የተጫነው ሕዝብ፣

      የክፉዎች ዘር፣ ብልሹ የሆኑ ልጆች ወዮላቸው!

      እነሱ ይሖዋን ትተዋል፤+

      የእስራኤልን ቅዱስ አቃለዋል፤

      ጀርባቸውን ሰጥተውታል።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ