14 ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት ሲመጣ የጴጥሮስ አማት+ ትኩሳት ይዟት ተኝታ አገኛት።+ 15 እጇንም ሲዳስሳት+ ትኩሳቱ ለቀቃት፤ ተነስታም ታገለግለው ጀመር። 16 ከመሸ በኋላ ሰዎች አጋንንት ያደሩባቸውን ብዙ ሰዎች ወደ እሱ አመጡ፤ መናፍስቱንም በአንድ ቃል አስወጣ፤ እየተሠቃዩ የነበሩትንም ሁሉ ፈወሰ፤ 17 ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ “እሱ ሕመማችንን ተቀበለ፤ ደዌያችንንም ተሸከመ” ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው።+