1 ነገሥት 8:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 አገልጋይህ ወደዚህ ስፍራ የሚያቀርበውን ጸሎት ለመስማት ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’+ ወዳልከው ወደዚህ ቤት ዓይኖችህ ቀንና ሌሊት ይመልከቱ።+ 1 ነገሥት 8:43 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት+ ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና እንዲፈሩህ+ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት። ማቴዎስ 21:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እንዲህም አላቸው፦ “‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል፤+ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አድርጋችሁታል።”+ ማርቆስ 11:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ሰዎቹንም ያስተምር ነበር፤ ደግሞም “‘ቤቴ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ አልተጻፈም?+ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት” አላቸው።+ ሉቃስ 19:46 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 46 እንዲህም አላቸው፦ “‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል’+ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት።”+
43 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት+ ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና እንዲፈሩህ+ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት።