የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 5:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  7 የሠራዊት ጌታ የይሖዋ የወይን እርሻ የእስራኤል ቤት ነውና፤+

      የይሁዳ ሰዎች እሱ ይወደው የነበረው የአትክልት ቦታ ናቸው።*

      ፍትሕን ሲጠብቅ+

      እነሆ፣ ግፍ ይፈጸማል፤

      ‘ጽድቅ ይሰፍናል’ ብሎ ሲጠብቅ

      እነሆ፣ የጭንቅ ጩኸት ይሰማል።”+

  • ኢሳይያስ 59:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 እውነት* ጠፍቷል፤+

      ከክፋት የራቀ ሁሉ ለጥፋት ተዳርጓል።

      ይሖዋ ይህን አየ፤ ደስም አልተሰኘም፤*

      ፍትሕ አልነበረምና።+

  • ኤርምያስ 5:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ወዲያና ወዲህ ተመላለሱ።

      ዙሪያውን ተመልከቱ፤ ልብ በሉ።

      ፍትሕን የሚያደርግ፣+

      ታማኝ መሆን የሚሻ ሰውም ታገኙ እንደሆነ

      በአደባባዮቿ ፈልጉ፤

      እኔም ይቅር እላታለሁ።

  • አሞጽ 6:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ፈረሶች በቋጥኝ ላይ ይሮጣሉ?

      ሰውስ እዚያ ላይ በከብት ያርሳል?

      እናንተ ፍትሕን ወደ መርዛማ ተክል፣

      የጽድቅንም ፍሬ ወደ ጭቁኝ* ለውጣችኋልና።+

  • ዕንባቆም 1:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ስለዚህ ሕግ ላልቷል፤

      ፍትሕም ጨርሶ የለም።

      ክፉው ጻድቁን ከቦታልና፤

      ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ተጣሟል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ