ማቴዎስ 11:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የምትሰሙትንና የምታዩትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፤+ 5 ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤+ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤+ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።+ የሐዋርያት ሥራ 10:37, 38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 37 ዮሐንስ ስለ ጥምቀት ከሰበከ በኋላ ከገሊላ አንስቶ በመላው ይሁዳ ይወራ ስለነበረው ጉዳይ ታውቃላችሁ፤+ 38 የተወራውም ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ ነው። አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ቀባው፤+ ደግሞም ኃይል ሰጠው፤ ኢየሱስም አምላክ ከእሱ ጋር ስለነበር መልካም ነገር እያደረገና+ በዲያብሎስ ቁጥጥር ሥር የወደቁትን እየፈወሰ+ በዚያ አገር ሁሉ ተዘዋወረ።
4 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የምትሰሙትንና የምታዩትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፤+ 5 ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤+ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤+ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።+
37 ዮሐንስ ስለ ጥምቀት ከሰበከ በኋላ ከገሊላ አንስቶ በመላው ይሁዳ ይወራ ስለነበረው ጉዳይ ታውቃላችሁ፤+ 38 የተወራውም ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ ነው። አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ቀባው፤+ ደግሞም ኃይል ሰጠው፤ ኢየሱስም አምላክ ከእሱ ጋር ስለነበር መልካም ነገር እያደረገና+ በዲያብሎስ ቁጥጥር ሥር የወደቁትን እየፈወሰ+ በዚያ አገር ሁሉ ተዘዋወረ።