3 “‘ባወጣኋቸው ደንቦች መሠረት ብትሄዱና ትእዛዛቴን ብትጠብቁ እንዲሁም ብትፈጽሙ+ 4 ዝናብን በወቅቱ አዘንብላችኋለሁ፤+ ምድሪቱም ምርቷን ትሰጣለች፤+ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጣሉ። 5 ገና እህላችሁን ወቅታችሁ ሳትጨርሱ ወይናችሁን የምትሰበስቡበት ጊዜ ይደርሳል፤ ገና ወይኑን ሰብስባችሁ ሳትጨርሱ ደግሞ ዘር የምትዘሩበት ጊዜ ይመጣል፤ ምግባችሁን እስክትጠግቡ ድረስ ትበላላችሁ፤ በምድራችሁም ያለስጋት ትቀመጣላችሁ።+