2 ነገሥት 17:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 14 እነሱ ግን አልሰሙም፤ በአምላካቸው በይሖዋ እንዳላመኑት አባቶቻቸው እነሱም ግትሮች ሆኑ።*+ ሆሴዕ 7:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ መሥክሮበታል፤+ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ አልተመለሱም፤+እሱንም አልፈለጉትም። አሞጽ 4:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ‘እኔም በከተሞቻችሁ ሁሉ አፋችሁን ባዶ አደረግኩት፤*በቤታችሁም ሁሉ የምትበሉት ነገር አሳጣኋችሁ፤+እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ። አሞጽ 5:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይሖዋን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤+አለዚያ በዮሴፍ ቤት ላይ ቁጣው እንደ እሳት ይነድዳል፤ቤቴልንም ይበላል፤ የሚያጠፋውም አይኖርም።
13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 14 እነሱ ግን አልሰሙም፤ በአምላካቸው በይሖዋ እንዳላመኑት አባቶቻቸው እነሱም ግትሮች ሆኑ።*+