1 ሳሙኤል 22:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ንጉሡም ዶይቅን+ “እንግዲያውስ አንተ ዙርና ካህናቱን ግደላቸው!” አለው። ኤዶማዊው+ ዶይቅም ወዲያውኑ ሄዶ ካህናቱን ገደላቸው። በዚያን ቀን፣ ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ የለበሱ 85 ሰዎችን ገደለ።+ 19 እንዲሁም የካህናቱን ከተማ ኖብን+ በሰይፍ መታ፤ ወንድም ሆነ ሴት፣ ልጅም ሆነ ጨቅላ ሕፃን፣ በሬም ሆነ አህያ ወይም በግ አንድም ሳያስቀር ሁሉንም በሰይፍ ገደለ።
18 ንጉሡም ዶይቅን+ “እንግዲያውስ አንተ ዙርና ካህናቱን ግደላቸው!” አለው። ኤዶማዊው+ ዶይቅም ወዲያውኑ ሄዶ ካህናቱን ገደላቸው። በዚያን ቀን፣ ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ የለበሱ 85 ሰዎችን ገደለ።+ 19 እንዲሁም የካህናቱን ከተማ ኖብን+ በሰይፍ መታ፤ ወንድም ሆነ ሴት፣ ልጅም ሆነ ጨቅላ ሕፃን፣ በሬም ሆነ አህያ ወይም በግ አንድም ሳያስቀር ሁሉንም በሰይፍ ገደለ።