25 በዚያ መኖር እንደጀመሩ አካባቢ ይሖዋን አይፈሩም ነበር። በመሆኑም ይሖዋ በመካከላቸው አንበሶችን ላከባቸው፤+ እነሱም የተወሰኑ ሰዎችን ገደሉ። 26 የአሦርም ንጉሥ እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “በግዞት ወስደህ በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ ያደረግካቸው ብሔራት የዚያች ምድር አምላክ እንዴት እንደሚመለክ አላወቁም። ስለዚህ በመካከላቸው አንበሶችን ላከባቸው፤ አንዳቸውም የዚያች ምድር አምላክ እንዴት እንደሚመለክ ስለማያውቁ አንበሶቹ እየገደሏቸው ነው።”