9 እንዲህም ሲል አዘዛቸው፦ “ይሖዋን በመፍራት በታማኝነትና በሙሉ ልብ ይህን ልታደርጉ ይገባል፦ 10 በየከተሞቻቸው የሚኖሩት ወንድሞቻችሁ ከደም መፋሰስ ጋር የተያያዘ ክስ+ አሊያም ከሕግ፣ ከትእዛዝ፣ ከሥርዓት ወይም ከድንጋጌዎች ጋር የተያያዘ ጥያቄ ይዘው በሚመጡበት ጊዜ ሁሉ በይሖዋ ፊት በደለኛ እንዳይሆኑ ልታስጠነቅቋቸው ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ግን በእናንተም ሆነ በወንድሞቻችሁ ላይ ቁጣው ይመጣል። በደለኛ እንዳትሆኑ ይህን ልታደርጉ ይገባል።