-
ኢሳይያስ 5:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 በግብዣቸው ላይ በገና፣ ባለ አውታር መሣሪያ፣
አታሞና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤
እነሱ ግን ይሖዋ ያከናወነውን ተግባር አያስቡም፤
የእጁንም ሥራ አይመለከቱም።
-
-
ኢሳይያስ 56:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 “ኑ! የወይን ጠጅ ላምጣና
እስኪወጣልን ድረስ እንጠጣ።+
ነገም እንደ ዛሬ ይሆናል፤ እንዲያውም በጣም የተሻለ ይሆናል።”
-
-
አሞጽ 6:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 የመንጋውን ጠቦቶች እንዲሁም የሰቡ ጥጃዎችን* እየበሉ+
ከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ ይተኛሉ፤+ በድንክ አልጋም ላይ ይንጋለላሉ፤+
-
ያዕቆብ 5:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 በምድር ላይ በቅንጦት ኖራችኋል፤ የራሳችሁንም ፍላጎት ለማርካት ትጥሩ ነበር። በእርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል።+
-
-
-