ዘዳግም 32:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 እነሱ ማመዛዘን የጎደለው* ብሔር ናቸው፤በመካከላቸውም ማስተዋል የሚባል ነገር የለም።+ ኢሳይያስ 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በሬ ጌታውን፣አህያም የባለቤቱን ጋጣ በሚገባ ያውቃል፤እስራኤል ግን እኔን* አላወቀም፤+የገዛ ሕዝቤም አላስተዋለም።” ኤርምያስ 4:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 “ሕዝቤ ሞኝ ነውና፤+እነሱ ለእኔ ትኩረት አይሰጡም። ማስተዋል የሌላቸው ቂል ልጆች ናቸው። ክፉ ነገር ለማድረግ ብልሃተኞች* ናቸው፤መልካም ነገር ማድረግ ግን አያውቁም።” ሆሴዕ 4:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ይጠፋል። እናንተ እውቀትን ስለናቃችሁ+እኔም ካህናት ሆናችሁ እንዳታገለግሉኝ እንቃችኋለሁ፤የአምላካችሁን ሕግ* ስለረሳችሁ+እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።
22 “ሕዝቤ ሞኝ ነውና፤+እነሱ ለእኔ ትኩረት አይሰጡም። ማስተዋል የሌላቸው ቂል ልጆች ናቸው። ክፉ ነገር ለማድረግ ብልሃተኞች* ናቸው፤መልካም ነገር ማድረግ ግን አያውቁም።”
6 ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ይጠፋል። እናንተ እውቀትን ስለናቃችሁ+እኔም ካህናት ሆናችሁ እንዳታገለግሉኝ እንቃችኋለሁ፤የአምላካችሁን ሕግ* ስለረሳችሁ+እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።