-
ኢሳይያስ 63:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
63 ይህ ከኤዶም የሚመጣው፣+
ደማቅ ቀለም ያለው* ልብስ ለብሶ ከቦስራ+ የሚገሰግሰው ማን ነው?
ይህ እጅግ ያማረ ልብስ ለብሶና
በታላቅ ኃይል ተሞልቶ የሚራመደው ማን ነው?
“በጽድቅ የምናገር፣
ለማዳን የሚያስችል ታላቅ ኃይል ያለኝ እኔ ነኝ።”
2 መጎናጸፊያህ የቀላውና
ልብሶችህ በመጭመቂያ ውስጥ ወይን እንደሚረግጥ ሰው ልብስ የሆኑት ለምንድን ነው?+
3 “በወይን መጭመቂያው ውስጥ ወይኑን ብቻዬን ረገጥኩ።
ከሕዝቦች መካከል ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም።
በቁጣዬም ረጋገጥኳቸው፤
በታላቅ ቁጣዬም ጨፈላለቅኳቸው።+
ደማቸውም ልብሶቼ ላይ ተረጨ፤
ልብሴንም ሁሉ በከልኩ።
-