17 ከዚያም የአሦር ንጉሥ ታርታኑን፣ ራብሳሪሱንና ራብሻቁን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ+ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ላካቸው።+ እነሱም ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ልብስ አጣቢው እርሻ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ በሚገኘው በላይኛው ኩሬ የውኃ መውረጃ ቦይ አጠገብ ቆሙ።+ 18 ንጉሡ እንዲመጣ በተጣሩ ጊዜ የንጉሡ ቤት ኃላፊ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣+ ጸሐፊው ሸብናህ+ እና ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአህ ወደ እነሱ ወጡ።