2 ነገሥት 18:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የእስራኤል ንጉሥ የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ+ ልጅ ሕዝቅያስ+ ነገሠ። 2 ነገሥት 18:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎች ያስወገደው፣+ የማምለኪያ ዓምዶቹን ያደቀቀውና+ የማምለኪያ ግንዱን* የቆራረጠው እሱ ነበር። በተጨማሪም ሙሴ ሠርቶት የነበረውን የመዳብ እባብ አደቀቀ፤+ የእስራኤል ሕዝብ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ለእባቡ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበርና፤ ይህም ጣዖት የመዳብ እባብ* ተብሎ ይጠራ ነበር። 2 ዜና መዋዕል 31:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ከዚህ በኋላ በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው በመላው ይሁዳና ቢንያም እንዲሁም በኤፍሬምና በምናሴ+ የነበሩትን የማምለኪያ ዓምዶች+ ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ግንዶቹን*+ ቆረጡ፤ ከፍ ያሉትንም የማምለኪያ ቦታዎችና+ መሠዊያዎቹን+ አፈራረሱ፤ ምንም ያስቀሩት ነገር አልነበረም፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየከተሞቻቸው፣ እያንዳንዳቸውም ወደየርስታቸው ተመለሱ።
4 ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎች ያስወገደው፣+ የማምለኪያ ዓምዶቹን ያደቀቀውና+ የማምለኪያ ግንዱን* የቆራረጠው እሱ ነበር። በተጨማሪም ሙሴ ሠርቶት የነበረውን የመዳብ እባብ አደቀቀ፤+ የእስራኤል ሕዝብ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ለእባቡ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበርና፤ ይህም ጣዖት የመዳብ እባብ* ተብሎ ይጠራ ነበር።
31 ከዚህ በኋላ በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው በመላው ይሁዳና ቢንያም እንዲሁም በኤፍሬምና በምናሴ+ የነበሩትን የማምለኪያ ዓምዶች+ ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ግንዶቹን*+ ቆረጡ፤ ከፍ ያሉትንም የማምለኪያ ቦታዎችና+ መሠዊያዎቹን+ አፈራረሱ፤ ምንም ያስቀሩት ነገር አልነበረም፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየከተሞቻቸው፣ እያንዳንዳቸውም ወደየርስታቸው ተመለሱ።