የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢያሱ 10:29, 30
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 ከዚያም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከመቄዳ ወደ ሊብና በመሄድ ሊብናን+ ወጓት። 30 ይሖዋም ከተማዋንና ንጉሥዋን+ በእስራኤላውያን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነሱም ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ በሰይፍ መቱ። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ እንዳደረጉትም ሁሉ በንጉሥዋ ላይ አደረጉ።+

  • 2 ነገሥት 8:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 ሆኖም ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው። ሊብናም+ በዚሁ ጊዜ ዓመፀ።

  • 2 ነገሥት 19:8-13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ራብሻቁም የአሦር ንጉሥ ለኪሶን+ ለቆ እንደሄደ ሲሰማ ወደ ንጉሡ ተመለሰ፤ ከሊብናም ጋር ሲዋጋ አገኘው።+ 9 ንጉሡ የኢትዮጵያው ንጉሥ ቲርሃቅ “ከአንተ ጋር ሊዋጋ ወጥቷል” የሚል ወሬ ሰምቶ ነበር። በመሆኑም ለሕዝቅያስ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት በድጋሚ መልእክተኞች ላከ፦+ 10 “የይሁዳን ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፦ ‘የምትታመንበት አምላክህ “ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትወድቅም” ብሎ አያታልህ።+ 11 እነሆ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን አገሮች ሁሉ ፈጽመው በማጥፋት ያደረጉትን ነገር ሰምተሃል።+ ታዲያ አንተ ብቻ ከዚህ የምታመልጥ ይመስልሃል? 12 አባቶቼ ያጠፏቸውን ብሔራት አማልክታቸው ታድገዋቸዋል? ጎዛን፣ ካራን፣+ ረጼፍና በቴልአሳር የነበሩት የኤደን ሕዝቦች የት አሉ? 13 የሃማት ንጉሥ፣ የአርጳድ ንጉሥ፣ የሰፋርዊም ከተሞች ንጉሥ እንዲሁም የሄና እና የኢዋ+ ነገሥታት የት አሉ?’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ