35 በዚያም ሌሊት የይሖዋ መልአክ ወጥቶ በአሦራውያን ሰፈር የነበሩትን 185,000 ሰዎች ገደለ።+ ሰዎችም በማለዳ ሲነሱ ሬሳውን አዩ።+ 36 በመሆኑም የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከዚያ ተነስቶ ወደ ነነዌ+ ተመለሰ፤ በዚያም ተቀመጠ።+ 37 ሰናክሬም በአምላኩ በኒስሮክ ቤት እየሰገደ ሳለ አድራሜሌክና ሳሬጸር የተባሉት የገዛ ልጆቹ በሰይፍ መትተው ገደሉት፤+ ከዚያም ወደ አራራት+ ምድር ሸሽተው ሄዱ። ልጁም ኤሳርሃደን+ በእሱ ምትክ ነገሠ።