17 ከዚያም ኤርምያስ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን ብትሰጥ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በሕይወት ትተርፋላችሁ።+ 18 ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን የማትሰጥ ከሆነ ግን ይህች ከተማ ለከለዳውያን አልፋ ትሰጣለች፤ እነሱም በእሳት ያቃጥሏታል፤+ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም።’”+