5 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እባክህ ዓይንህን አንስተህ ወደ ሰሜን ተመልከት” አለኝ። ስለዚህ ወደ ሰሜን ተመለከትኩ፤ በዚያም ከመሠዊያው በር በስተ ሰሜን በኩል መግቢያው ላይ ይህ የቅናት ምልክት ነበር። 6 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ከመቅደሴ እንድርቅ የሚያደርጉ ነገሮች+ ይኸውም የሚፈጽሟቸውን አስከፊና አስጸያፊ ነገሮች ትመለከታለህ?+ ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮችን ገና ታያለህ።”