ኤርምያስ 23:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 “ከዚያም የቀሩትን በጎቼን ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደ መሰማሪያቸውም መልሼ አመጣቸዋለሁ፤+ እነሱም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ደግሞም ይበዛሉ።+ ኤርምያስ 23:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በእሱ ዘመን ይሁዳ ይድናል፤+ እስራኤልም ያለስጋት ይኖራል።+ የሚጠራበትም ስም ‘ይሖዋ ጽድቃችን ነው’ የሚል ይሆናል።”+ ኤርምያስ 33:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 በዚያ ዘመን ይሁዳ ትድናለች፤+ ኢየሩሳሌምም ያለስጋት ትቀመጣለች።+ እሷም “ይሖዋ ጽድቃችን ነው” ተብላ ትጠራለች።’”+ ሕዝቅኤል 34:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ አደገኛ የሆኑ የዱር አራዊትንም ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ፤+ በመሆኑም በምድረ በዳ ያለስጋት ይኖራሉ፤ በጫካዎችም ውስጥ ይተኛሉ።+
3 “ከዚያም የቀሩትን በጎቼን ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደ መሰማሪያቸውም መልሼ አመጣቸዋለሁ፤+ እነሱም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ደግሞም ይበዛሉ።+
25 “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ አደገኛ የሆኑ የዱር አራዊትንም ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ፤+ በመሆኑም በምድረ በዳ ያለስጋት ይኖራሉ፤ በጫካዎችም ውስጥ ይተኛሉ።+