2 ነገሥት 10:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ የሬካብን+ ልጅ ኢዮናዳብን+ ወደ እሱ ሲመጣ አገኘው። ኢዩም ሰላምታ ሰጥቶት* “የእኔ ልብ ከልብህ ጋር እንደሆነው ሁሉ የአንተስ ልብ ሙሉ በሙሉ* ከእኔ ጋር ነው?” አለው። ኢዮናዳብም “አዎ ነው” ሲል መለሰለት። ኢዩም “እንደዚያ ከሆነ እጅህን ስጠኝ” አለው። እሱም እጁን ሰጠው፤ ኢዩም ጎትቶ ወደ ሠረገላው አወጣው። 1 ዜና መዋዕል 2:55 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 55 በያቤጽ የሚኖሩት የጸሐፍት ወገኖች ቲራታውያን፣ ሺመአታውያን እና ሱካታውያን ነበሩ። እነዚህ የሬካብ+ ቤት አባት ከሆነው ከሃማት የተገኙት ቄናውያን+ ናቸው።
15 ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ የሬካብን+ ልጅ ኢዮናዳብን+ ወደ እሱ ሲመጣ አገኘው። ኢዩም ሰላምታ ሰጥቶት* “የእኔ ልብ ከልብህ ጋር እንደሆነው ሁሉ የአንተስ ልብ ሙሉ በሙሉ* ከእኔ ጋር ነው?” አለው። ኢዮናዳብም “አዎ ነው” ሲል መለሰለት። ኢዩም “እንደዚያ ከሆነ እጅህን ስጠኝ” አለው። እሱም እጁን ሰጠው፤ ኢዩም ጎትቶ ወደ ሠረገላው አወጣው።
55 በያቤጽ የሚኖሩት የጸሐፍት ወገኖች ቲራታውያን፣ ሺመአታውያን እና ሱካታውያን ነበሩ። እነዚህ የሬካብ+ ቤት አባት ከሆነው ከሃማት የተገኙት ቄናውያን+ ናቸው።