10 በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹን ልኮ በይሖዋ ቤት ካሉት ውድ ዕቃዎች+ ጋር ወደ ባቢሎን አመጣው።+ የአባቱን ወንድም ሴዴቅያስንም በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።+
11 ሴዴቅያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 21 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ።+ 12 በአምላኩ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። በይሖዋ ትእዛዝ በተናገረው በነቢዩ ኤርምያስ ፊት ራሱን ዝቅ አላደረገም።+