-
ኤርምያስ 21:8-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 “ደግሞም ይህን ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አድርጌአለሁ። 9 በዚህች ከተማ የሚቀሩ ሰዎች በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ይሞታሉ። ይሁንና ከከተማዋ ወጥቶ፣ ለከበቧችሁ ከለዳውያን እጁን የሚሰጥ በሕይወት ይኖራል፤ ሕይወቱም* እንደ ምርኮ ትሆንለታለች።”’*+
10 “‘“መልካም ነገር ሳይሆን ጥፋት ለማምጣት ፊቴን ወደዚህች ከተማ አዙሬአለሁና”+ ይላል ይሖዋ። “ለባቢሎን ንጉሥ ትሰጣለች፤+ እሱም በእሳት ያቃጥላታል።”+
-