-
ኤርምያስ 44:12-14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 በግብፅ ምድር ለመኖር ወደዚያ ለመሄድ ቆርጠው የተነሱትንም የይሁዳ ቀሪዎች እወስዳለሁ፤ ሁሉም በግብፅ ምድር ይጠፋሉ።+ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ከትንሹ እስከ ትልቁ ድረስ በረሃብ ያልቃሉ፤ በሰይፍና በረሃብ ይሞታሉ። ለእርግማን፣ ለውርደትና ለነቀፋ ይዳረጋሉ፤ መቀጣጫም ይሆናሉ።+ 13 ኢየሩሳሌምን እንደቀጣሁ ሁሉ በግብፅ ምድር የሚኖሩትንም በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* እቀጣለሁ።+ 14 በግብፅ ምድር ለመኖር የሄዱት የይሁዳ ቀሪዎችም አምልጠው ወይም በሕይወት ተርፈው ወደ ይሁዳ ምድር አይመለሱም። ወደዚያ ለመመለስና በዚያ ለመኖር ቢመኙም እንኳ* ከጥቂት ሰዎች በስተቀር አምልጦ የሚመለስ አይኖርም።’”
-