2 ዜና መዋዕል 24:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ይሖዋ ወደ እሱ እንዲመልሷቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ እነሱም ያስጠነቅቋቸው* ነበር፤ ሕዝቡ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልነበረም።+ ነህምያ 9:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+ ዘካርያስ 7:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እነሱ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆኑም፤+ በግትርነትም ጀርባቸውን ሰጡ፤+ ላለመስማትም ሲሉ ጆሯቸውን ደፈኑ።+
26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+