10 ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን እጠራዋለሁ፤+ ዙፋኑንም እኔ ከሸሸግኳቸው ከእነዚህ ድንጋዮች በላይ አስቀምጣለሁ፤ ንጉሣዊ ድንኳኑንም በእነሱ ላይ ይዘረጋል።+ 11 እሱም መጥቶ የግብፅን ምድር ይመታል።+ ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ ለገዳይ መቅሰፍት፣ በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ለምርኮ እንዲሁም ሰይፍ የሚገባው ሁሉ ለሰይፍ ይሰጣል።+