-
ኤርምያስ 36:22-24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 ንጉሡ በዘጠነኛው ወር* የክረምቱን ወቅት በሚያሳልፍበት ቤት ተቀምጦ ነበር፤ በፊቱም በምድጃ የሚነድ እሳት ነበር። 23 የሁዲ ሦስት ወይም አራት ዓምድ ካነበበ በኋላ ንጉሡ የተነበበውን ክፍል በጸሐፊ ቢላ እየቀደደ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ይወረውረው ነበር፤ ጥቅልሉ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ እስኪያልቅ ድረስ እንዲሁ አደረገ። 24 ይህን ሁሉ ቃል ሲሰሙ የነበሩት ንጉሡም ሆነ አገልጋዮቹ በሙሉ ምንም ፍርሃት አልተሰማቸውም፤ ልብሳቸውንም አልቀደዱም።
-