ኢሳይያስ 1:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤+ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አስወግዱ፤መጥፎ ድርጊት መፈጸማችሁን አቁሙ።+ ሕዝቅኤል 18:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ ከራሳችሁ ላይ አስወግዱ፤+ ደግሞም አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ይኑራችሁ፤*+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለምን ትሞታላችሁ?’+