24 እነሱም ወደ እስራኤል ሰፈር ሲመጡ እስራኤላውያን ተነስተው ሞዓባውያንን መምታት ጀመሩ፤ እነሱም ከፊታቸው ሸሹ።+ እስራኤላውያንም ሞዓባውያንን እየመቱ ወደ ሞዓብ ገሰገሱ። 25 ከተሞቹንም ደመሰሱ፤ እያንዳንዱም ሰው ድንጋይ እየጣለ ጥሩውን መሬት ሁሉ በድንጋይ ሞላው፤ የውኃ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤+ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቆረጡ።+ በመጨረሻም የቂርሃረሰት+ የድንጋይ ግንቦች ብቻ ቆመው ቀሩ፤ ወንጭፍ የሚወነጭፉትም ዙሪያዋን ከበው መቷት።