-
ኤርምያስ 39:4-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ፣ በንጉሡ የአትክልት ቦታ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ከከተማዋ ወጥተው ሸሹ፤+ ወደ አረባ የሚወስደውንም መንገድ ተከትለው ሄዱ።+ 5 የከለዳውያን ሠራዊት ግን አሳደዳቸው፤ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት።+ ከያዙት በኋላ በሃማት+ ምድር በሪብላ+ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነጾር* አመጡት፤ እሱም በዚያ ፈረደበት። 6 የባቢሎን ንጉሥ በሪብላ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አሳረዳቸው፤ በተጨማሪም የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ታላላቅ ሰዎች ሁሉ አሳረደ።+ 7 የሴዴቅያስንም ዓይን አሳወረ፤ ከዚያም ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በመዳብ የእግር ብረት አሰረው።+
-