የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 7:15-20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 እሱም ሁለቱን ዓምዶች+ ከቀለጠ መዳብ ሠራ፤ እያንዳንዱም ዓምድ ቁመቱ 18 ክንድ ነበር፤ ሁለቱ ዓምዶች እያንዳንዳቸው በመለኪያ ገመድ ሲለኩ መጠነ ዙሪያቸው 12 ክንድ ነበር።+ 16 እንዲሁም በዓምዶቹ አናት ላይ የሚሆኑ ሁለት የዓምድ ራሶችን ከመዳብ ሠራ። የአንደኛው የዓምድ ራስ ቁመት አምስት ክንድ የሌላኛው የዓምድ ራስ ቁመትም አምስት ክንድ ነበር። 17 በእያንዳንዱ ዓምድ አናት ላይ ያለው የዓምድ ራስ በሰንሰለት ጉንጉን የተሠሩ መረቦች ነበሩት፤+ በአንደኛው የዓምድ ራስ ላይ ሰባት በሌላኛው የዓምድ ራስ ላይም ሰባት ነበሩ። 18 በዓምዶቹ አናት ላይ ያሉትን የዓምድ ራሶች ለማስጌጥ በአንደኛው መረብ ዙሪያ ሮማኖችን በሁለት ረድፍ ሠራ፤ በሁለቱም የዓምድ ራሶች ላይ እንዲሁ አደረገ። 19 በረንዳው አጠገብ በሚገኙት ዓምዶች አናት ላይ ያሉት የዓምድ ራሶች አራት ክንድ ቁመት ያለው የአበባ ቅርጽ ነበራቸው። 20 የዓምድ ራሶቹ በሁለቱ ዓምዶች ላይ፣ ልክ ከመረብ ሥራው ቀጥሎ ካለው ከሆዱ በላይ ነበሩ፤ በእያንዳንዱ የዓምድ ራስ ዙሪያ 200 ሮማኖች በረድፍ ተደርድረው ነበር።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ