21 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል። በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ+ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’ በማለት ይጠይቃሉ።+ 22 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን+ የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ትተው+ ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ለእነሱ ስለሰገዱ እንዲሁም እነሱን ስላገለገሉ ነው።+ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣባቸው ለዚህ ነው።’”+