10 እኔም ገብቼ አየሁ፤ መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታትንና የሚያስጠሉ አራዊትን+ ሁሉ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ የእስራኤል ቤት ጣዖቶችን ሁሉ ምስል+ ተመለከትኩ፤ ምስላቸውም በግድግዳው ዙሪያ ተቀርጾ ነበር። 11 ደግሞም 70 የሚሆኑ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በምስሎቹ ፊት ቆመው ነበር፤ የሳፋን+ ልጅ ያአዛንያህ በመካከላቸው ቆሞ ነበር። እያንዳንዳቸውም በእጃቸው ጥና የያዙ ሲሆን መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጭስም እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር።+