የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 4:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 እንዲሁም ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ይኸውም የሰማይን ሠራዊት በሙሉ በምታይበት ጊዜ ተታለህ እንዳትሰግድላቸውና እንዳታገለግላቸው።+ እነዚህ አምላክህ ይሖዋ ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸው ናቸው።

  • 2 ነገሥት 17:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 የአምላካቸውን የይሖዋን ትእዛዛት በሙሉ ተዉ፤ ለራሳቸውም ከብረት የተሠሩ ሁለት የጥጃ ሐውልቶችን* አበጁ፤+ የማምለኪያም ግንድ*+ ሠሩ፤ ለሰማያት ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፤+ እንዲሁም ባአልን አገለገሉ።+

  • 2 ነገሥት 21:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 ምናሴ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 12 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ55 ዓመት ገዛ።+ የእናቱ ስም ሄፍጺባ ነበር።

  • 2 ነገሥት 21:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 አባቱ ሕዝቅያስ አስወግዷቸው የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች መልሶ ገነባ፤+ እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለባአል መሠዊያዎችን አቆመ፤+ የማምለኪያ ግንድም* ሠራ።+ ለሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ሰገደ፤ እነሱንም አገለገለ።+

  • ኤርምያስ 19:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ‘የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፣ አዎ በጣሪያዎቻቸው ላይ ለሰማያት ሠራዊት መሥዋዕቶች ያቀረቡባቸውና+ ለሌሎች አማልክት የመጠጥ መባዎች ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ+ እንደዚህ ስፍራ፣ እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።’”+

  • ሕዝቅኤል 8:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 በመሆኑም ወደ ይሖዋ ቤት ውስጠኛው ግቢ+ አመጣኝ። በዚያም በይሖዋ ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ በበረንዳውና በመሠዊያው መካከል 25 ያህል ወንዶች ነበሩ፤ እነሱም ጀርባቸውን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ ሰጥተው ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ነበር፤ ደግሞም በምሥራቅ አቅጣጫ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።+

  • ሶፎንያስ 1:4, 5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 “በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ላይ

      እጄን እዘረጋለሁ፤

      የባአልን ቀሪዎች* ሁሉና የባዕድ አምላክ ካህናትን ስም

      ከሌሎቹ ካህናት ጋር ከዚህ ስፍራ ፈጽሜ አስወግዳለሁ፤+

       5 በቤት ጣሪያዎች ላይ ሆነው ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትን+

      እንዲሁም በአንድ በኩል ለይሖዋ እየሰገዱና ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል እየገቡ+

      በሌላ በኩል ግን ለማልካም ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል የሚገቡትን አጠፋለሁ፤+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ