ነህምያ 9:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ለመስማትም አሻፈረኝ አሉ፤+ በመካከላቸው የፈጸምካቸውን እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች ረሱ፤ ከዚህ ይልቅ ግትሮች ሆኑ፤* በግብፅ ወደነበሩበት የባርነት ሕይወት ለመመለስም መሪ ሾሙ።+ አንተ ግን ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆንክ፣* ሩኅሩኅ፣* መሐሪ፣ ለቁጣ የዘገየህና ታማኝ ፍቅርህ የበዛ* አምላክ ነህ፤+ እነሱንም አልተውካቸውም።+ ነህምያ 9:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ወደ ሕግህ እንዲመለሱ ለማድረግ ብታስጠነቅቃቸውም እነሱ ግን እብሪተኞች በመሆን ትእዛዛትህን ለመስማት አሻፈረኝ አሉ፤+ ለሚጠብቃቸው ሰው ሁሉ ሕይወት በሚያስገኙት ድንጋጌዎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ።+ ደግሞም በግትርነት ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውን አደነደኑ፤ ለመስማትም አሻፈረኝ አሉ። ዘካርያስ 7:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ልባቸውን እንደ አልማዝ* አጠነከሩ፤+ እንዲሁም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት፣ በቀድሞዎቹ ነቢያት በኩል የላከውን ሕግና* ቃል አልታዘዙም።+ ከዚህም የተነሳ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እጅግ ተቆጣ።”+
17 ለመስማትም አሻፈረኝ አሉ፤+ በመካከላቸው የፈጸምካቸውን እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች ረሱ፤ ከዚህ ይልቅ ግትሮች ሆኑ፤* በግብፅ ወደነበሩበት የባርነት ሕይወት ለመመለስም መሪ ሾሙ።+ አንተ ግን ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆንክ፣* ሩኅሩኅ፣* መሐሪ፣ ለቁጣ የዘገየህና ታማኝ ፍቅርህ የበዛ* አምላክ ነህ፤+ እነሱንም አልተውካቸውም።+
29 ወደ ሕግህ እንዲመለሱ ለማድረግ ብታስጠነቅቃቸውም እነሱ ግን እብሪተኞች በመሆን ትእዛዛትህን ለመስማት አሻፈረኝ አሉ፤+ ለሚጠብቃቸው ሰው ሁሉ ሕይወት በሚያስገኙት ድንጋጌዎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ።+ ደግሞም በግትርነት ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውን አደነደኑ፤ ለመስማትም አሻፈረኝ አሉ።
12 ልባቸውን እንደ አልማዝ* አጠነከሩ፤+ እንዲሁም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት፣ በቀድሞዎቹ ነቢያት በኩል የላከውን ሕግና* ቃል አልታዘዙም።+ ከዚህም የተነሳ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እጅግ ተቆጣ።”+