ዘዳግም 32:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ምክንያቱም ቁጣዬ እሳት አቀጣጥሏል፤+እሱም እስከ መቃብር* ጥልቀት ድረስ ዘልቆ ይነድዳል፤+ምድርንና ምርቷን ይበላል፤የተራሮችንም መሠረት ያቃጥላል። ኢሳይያስ 1:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ብርቱውም ሰው እንደ ተልባ እግር* ይሆናል፤የሥራውም ውጤት እንደ እሳት ብልጭታ ይሆናል፤ሁለቱም አብረው ይቃጠላሉ፤እሳቱንም ማጥፋት የሚችል ማንም የለም።” ኤርምያስ 7:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ንዴቴና ቁጣዬ በዚህ ቦታ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በዱር ዛፎችና በምድሪቱ ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤+ ቁጣዬ ይነድዳል፤ ፈጽሞም አይጠፋም።’+
20 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ንዴቴና ቁጣዬ በዚህ ቦታ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በዱር ዛፎችና በምድሪቱ ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤+ ቁጣዬ ይነድዳል፤ ፈጽሞም አይጠፋም።’+