24 “‘“ይሁን እንጂ በሚገባ ብትታዘዙኝ” ይላል ይሖዋ፣ “በሰንበትም ቀን በከተማዋ በሮች ሸክም ይዛችሁ ባትገቡና በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሥራ ባለመሥራት ቀኑን ብትቀድሱት፣+ 25 በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መኳንንት+ ይኸውም እነሱና መኳንንታቸው እንዲሁም የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤+ ይህችም ከተማ ለዘለቄታው የሰው መኖሪያ ትሆናለች።