ዘዳግም 29:24-26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 እነሱም ሆኑ ሁሉም ብሔራት ‘ይሖዋ በዚህች ምድር ላይ እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?+ ይህን ታላቅ ቁጣስ ምን አመጣው?’ ይላሉ። 25 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ከግብፅ ምድር ባወጣቸው+ ጊዜ ከእነሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን በማፍረሳቸው ነው።+ 26 ሄደውም ሌሎችን አማልክት ይኸውም የማያውቋቸውንና እሱ እንዲያመልኳቸው ያልፈቀደላቸውን* አማልክት አገለገሉ፤ ደግሞም ሰገዱላቸው።+ 1 ነገሥት 9:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል።+ በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’+ በማለት ያፏጫሉ። 9 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው አባቶቻቸውን ከግብፅ ምድር ያወጣውን አምላካቸውን ይሖዋን ትተው ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ለእነሱ ስለሰገዱ እንዲሁም እነሱን ስላገለገሉ ነው። ይሖዋ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣባቸው ለዚህ ነው።’”+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 2:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በማሾፍ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል።+ “‘ፍጹም ውበት የተላበሰችና የምድር ሁሉ ደስታ’+ በማለት ይጠሯት የነበረችው ከተማ ይህች ናት?” እያሉ በመገረም በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፏጫሉ፤+ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ።
24 እነሱም ሆኑ ሁሉም ብሔራት ‘ይሖዋ በዚህች ምድር ላይ እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?+ ይህን ታላቅ ቁጣስ ምን አመጣው?’ ይላሉ። 25 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ከግብፅ ምድር ባወጣቸው+ ጊዜ ከእነሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን በማፍረሳቸው ነው።+ 26 ሄደውም ሌሎችን አማልክት ይኸውም የማያውቋቸውንና እሱ እንዲያመልኳቸው ያልፈቀደላቸውን* አማልክት አገለገሉ፤ ደግሞም ሰገዱላቸው።+
8 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል።+ በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’+ በማለት ያፏጫሉ። 9 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው አባቶቻቸውን ከግብፅ ምድር ያወጣውን አምላካቸውን ይሖዋን ትተው ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ለእነሱ ስለሰገዱ እንዲሁም እነሱን ስላገለገሉ ነው። ይሖዋ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣባቸው ለዚህ ነው።’”+
15 በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በማሾፍ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል።+ “‘ፍጹም ውበት የተላበሰችና የምድር ሁሉ ደስታ’+ በማለት ይጠሯት የነበረችው ከተማ ይህች ናት?” እያሉ በመገረም በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፏጫሉ፤+ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ።